Image placeholder
የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በወቅታዊ ጉዳዮች እና መደበኛ ተግባራትን ያሉበትን ሁኔታ ገምግሟል።
By Belay | 2023-08-27

አስተዳደሩ የ5 ወራት የክህሎት መር የስራ ዕድል ፈጠራ ዕቅድ ሁኔታ የጸጋ ልየት ፣ የተፈጠሩ የስራ ዕድሎች የክፍለ ከተማ ሴክተር ጽ/ቤቶችና ወረዳዎች የፈጠሩት የስራ ዕድል የተገመገመ ሲሆን ፣ " ጳጉሜን ለኢትዮጵያ" በሚል ሃሳብ የጳጉሜን ቀናት በተለያዩ ስያሜዎችና የሚከናወኑ ተግባራትን ፣ "ትምህርት ለትውልድ " በሚል መሪ ቃል በክፍለ ከተማው የሚገኙ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ደረጃቸውን የማሻሻል ስራዎች ፣ በወቅታዊ ሰላምና ጸጥታ ስራዎች እንዲሁም የ2016 ዓ.ም የዘመን መለወጫ ምክንያት በማድረግ በክፍለ ከተማው የማዕድ ማጋራትና ዕቅድን እና የኑሮ ውድነት ለመከላከል እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራትን ገምግሟል።

በውይይት መድረኩ የተገኙት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ በሁሉም ወረዳዎች የተሰሩትን ስራዎች በማጎልበትና ሙሉ አቅምን ተጠቅሞ ወደ ስራ መግባትና የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በዘላቂነት መፍታት ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት የሚገባቸው ጉዳዮች ናቸው ብለዋል፡፡

የጉለሌ ክፍለ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ይከበር ስማቸው በበኩላቸው የብልጽግና ፓርቲ ለዜጎች የስራ ዕድል መፍጠር በመሆኑ ሁሉም አመራር ትኩረት በመስጠት ስራ ስራዎችን ቆጥረን መስጠትና በመረከብ ብልሹ አሰራርን በመታገል የነዋሪዎችን ጥያቄ መመለስ ይገባል ብለዋል፡፡

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ እና የስራ፣ኢንዱስትሪና ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰሎሞን ታደሰ የስራ ዕድል ፈጠራ ን የተለያዩ አደረጃጀት ላይ ያሉ መዋቅሮችን ተጠቅሞ ከመፈተሽ ባለፈ የሚፈጠሩ የስራ እድሎችን ቅሬታዎችን በማይፈጥር መልኩ ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ተጠቃሚ የማድረግ ስራችን አጠናክረን ማስቀጠል ይገባል ብለዋል፡፡

በስራ እድል ፈጠራ ዘርፉ የሚታዩ ክፍተቶችን በመለየት የክህሎት፣ የገበያ ትስስርና የመስሪያ ቦታ ችግሮችን መፍታት ላይ በቀጣይ ትኩረት ተሰጥቶ የሚሰራባቸው ጉዳዮች ናቸው ፡፡

የቅርብ ዜና


Loading...