Image placeholder
የምትተክል ሀገር የሚፀና ትውልድ የአረንጓዴ አሻራ የንቄናቄ መርሀ ግብር በጉለሌ ክፍለ ከተማ በወረዳ 1 አስተዳደር በደመቀ ሁኔታ ተካሂዷል !!
By web admin | 2024-06-29

የምትተክል ሀገር የሚፀና ትውልድ የአረንጓዴ አሻራ የንቄናቄ መርሀ ግብር በጉለሌ ክፍለ ከተማ በወረዳ 1 አስተዳደር በደመቀ ሁኔታ ተካሂዷል !!

በመርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት አቶ ይከበር ስማቸው እንደገለፁት ኢትዮጵያ ከለውጡ በኋላ በየአመቱ በርካታ ችግኞችን በመትከል ለአለም የአየር ንብረት መሻሻል የበኩሏን ድርሻ በመወጣትና ግሪን ለጋሴን እውን በማድረግ ፈር ቀዳጅ የሆነች ሀገር እንደመሆኗ መጠን በዚህ ቀጀት አመትም እንደ ሀገር የምንተክለውን ችግኝ በተሳካ ሁኔታ ለማጠናቀቅና እቅዳችንን ለማሳካት የቅዴመ ተከላ ዝግጅት በተገቢው መንገድ መስራት አስፈላጊ በመሆኑ መላው የክፍለ ከተማችን ነዋሪ የፓርቲያችን አባላት በየደረጃው የሚገኙ የግልና የሀይማኖት ተቋማት የመንግስት ሰራተኞች ተማሪዎች መምህራን ሁሉም በጋራ በቂ ጉድጓድ በመቆፈር ለመጪው ትውልድ የምትመች ሀገርና ከተማ በመፍጠር የጋራ ትርክት መገንባት ላይ እንዲረባረቡ አደራ በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተገኝ ወዛ በበኩላቸው የአረንጓዴ አሻራ እውን እንዲሆን ከመላ ህዝባችንና ከወረዳው ነዋሪ ጋር በጋራ በመስራት መሰረታዊ የሆነ ለውጥ ለማምጣት ዝግጁ ነን ያሉ ሲሆን በአንድ ማዕከል ከምንቆፍረው በተጨማሪ ሁሉም በየግቢውና በየአካባቢው ለተከላ የሚሆን ጉድጓድ እንዲያዘጋጅ መደረግ አለበት ብለዋል።

በመጨረሻም ከ4,000 በላይ ህዝብ የተሳተፈበት የጉድጓድ ቁፋሮ ስራ ተሰርቷል።

የቅርብ ዜና


Loading...