Image placeholder
ምንም እንኳን የተለያየ የፖለቲካ አይዲዮሎጂ ቢኖረንም ለኢትዮጵያ ከፍታ ሲባል በጋራ ቆመን በአንድነት ሰርተን ሁለተናዊ ለውጥ ማምጣት ይጠበቅብናል ተባለ !!
By Belay | 2024-06-25

ምንም እንኳን የተለያየ የፖለቲካ አይዲዮሎጂ ቢኖረንም ለኢትዮጵያ ከፍታ ሲባል በጋራ ቆመን በአንድነት ሰርተን ሁለተናዊ ለውጥ ማምጣት ይጠበቅብናል ተባለ !!

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ወልዴ ወገሴ ለተፎካካሪ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በ2016በጀት አመት አስተዳደሩ የሰራቸውን ዘርፈ ብዙ ተግባራት በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን ምክር ቤቱ ጠንካራ ከሆነ ለክፍለ ከተማው ለውጥ ለአንድ ሀገር ልማትና ዓላማ መሳካት ትልቅ አቅም መሆን በመረዳትና አዲስ አበባ ከኢትዮጵያ ከተሞች ውጪ ለውጪ ሀገራት አቻ ከተሞች ልምድ እያካፈለች ነው ብለዋል። ከለውጡ በኋላ ከማሳደድ በመላቀቅ የፖለቲካ ባህላችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገና ቅርርባችን እየተጠናከረ ልምድ እየሆነ መምጣቱን አንስተው ሁሉም የተፎካካሪ ፓርቲ እኛን ጨምሮ አባሎቻችን ላይ ስለ ሀገር ግንባታና በኢኮኖሚ ስለምናመጣው ለውጥ ስለ ሰላምና ፀጥታ በቂ ስራ መስራት በቀጣይም አስተዳደሩ በሚያከናውናቸው ተግባራት መረባረብ ያስፈልጋል ብለዋል።

በውይይቱ ላይ የተገኙት የጉለሌ ክፍለ ከተማ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ይከበር ስማቸው በበኩላቸው በሀገሪቱ የተለያየ ፓርቲ ተቋም የሚመሰረተው ኢትዮጵያ ለማሻገርና ለትውልዱ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ካልሆነ የባሰ ተግዳሮት እንዳይገጥመን የሚመሰረቱ ፓርቲዎችን በአግባቡ ማኔጅ ማድረግ ወንድማማችነትና እህትማማችነትን ማጉላት ያስፈልጋል ያሉ ሲሆን የጋራ ግንዛቤ ለመያዝ የጋራ ተግባቦት ለመፍጠር የተሰሩ ስራዎችን መጎብኘት ማየት እና ማገዝ እንዳለ ሆኖ ሌብነትና ብልሹ አሰራር ላይ በጋራ ታግለን መረጃዎችን በአግባቡ መቀያየር በህጉ መሰረት ተፈፃሚ እንዲሆን ማድረግ ይጠበቅብናል ብለዋል።

የክፍለ ከተማው የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ ወ/ሮ ገነት ዋቅጋሪ በበኩላቸው የጋራ ምክር ቤቱ በስም ደረጃ መቅረት የለበትም በዚህ ዓመት በተጀመረው ልክ አጠናክሮ መቀጠል ያስፈልጋል ስራዎችን በዚህ ልክ ገምግመን ለቀጣይ ደግሞ የትኩረት አቅጣጫ አስቀምጠን በእቅድ መመራት ተገቢ ነው ከውጪ ሆኖ ከመተቻቸት ለወከለን ህዝብ በታማኝነት ማገልገል ለበለጠ ውጤት መነሳሳት የበኩሉን ሚና ይኖረዋል በማለት ቀጣይ በርካታ የሚሰሩ ስራዎች ስላሉ በክረምት መርሀ ግብር የተያዙ ለአብነት ችግኝ ተከላ የቤት እድሳት የሰላምና ፀጥታ እንዲሁም ሌሎች ተግባራቶች ላይ አብሮ መቆም ያስፈልጋል ብለዋል።

በውይይቱ ወቅት "ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ከተነሱ ሀሳቦች መካከል"ጉለሌ ክፍለ ከተማ ከጋራ ምክርቤቱ ጋር ተቀራርቦ በመስራት ሞዴል ነው ያሉ ሲሆን በተለይ ለወጣት አመራሮች እድል በመሰጠቱ በርካታ ስራዎች ተሰርተዋል ለዚህ ደግሞ ትልቁ ነገር በጀት አጠቃቀምን በአግባቡ በመምረት ለታለመለት አላማ በማዋላችሁ ስራው ላይ ጥራት ፍጥነት ብዛት በአንድ ላይ አብረው እንዲጓዙ አድርጋችኋል ብለዋል።አስተዳደሩ በቀጣይ ቢሰራቸው ካሏቸው ሀሳቦች መካከል አዲዲስ ፕሮጀክቶችን ሲሰራ የአካል ጉዳተኞች መሸጋገሪያ ታሳቢ ያደረገ እንዲሆንና ወጣቶች ላይ ደግሞ አሁን በጀመረው አግባብ የተጠቃሚነት ስራው ላይ አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።

የቅርብ ዜና


Loading...