Image placeholder
''በወጣቶች ንቁ ተሳትፎ ህብረ ብሔራዊነታችን ይረጋገጣል'' በሚል መሪ ቃል ለ4ኛ ጊዜ የክበባት ውድድር ፌስቲቫል ተዘጋጅቷል።
By web admin | 2023-08-27

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት በክፍለ ከተማው በሚገኙ 12 የወጣቶች ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት የሚሠጡ አገልግሎቶችን የማስተዋወቅ እና የበጋ ታዳጊ፣ወጣቶችና የክበባት ውድድር ፌስቲቫል አዘጋጅቷል።

ፕሮግራም ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የክፍለ ከተማው ዲሞክራሲና ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ይከበር ስማቸው እንደገለፁት ክፍለ ከተማው ከዚህ በፊት በዘርፋ ሀገር አቀፍ ባለተሰጥዖ ስፖርተኞች መፍለቂያ መሆኑን የዛሬው በሁሉ ወጣቶች ስብዕና መገንቢያ ማዕከሎቻችን በበጋ ወራት ሰልጥነው በውድድር መንፈስ ልምድ ልውውጥ ያደረጉበት መድረክ ማሣያ በመሆኑ አስተዳደሩ ለዘርፉ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ይገኛል ብለዋል።

የክፍለ ከተማው ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መሠለ ይትባረክ በበኩላቸው የክፍለ ከተማው ማህበረሰብ ስብዕና መገንቢያ ማዕከሎቻችን የሚሰጡትን አገልግሎቶች በማስገንዘብ ተጠቃሚ የሆኑ ክበባትና ታዳጊ ስፖርተኞች ያሉበትን ደረጃ በመመዘን የውድድር መንፈስ በማላበስ የእርስ በእርስ ልምድ ልውውጥን ያለመ ነው ብለዋል።

ፌስቲቫሉ በማዕከሎቹ ሲጠቀሙ በነበሩ ታዳጊ ወጣቶችና ክበባት በተለያዪ የስፖርት አይነት ውድድር አድርጎ የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ ስፖርተኞችና ማህበራት ከ1እስከ3 ለወጡ የገንዘብና እውቅና ሰርተፍኬት በመስጠት ፕሮግራሙ ተጠቃሏል

የቅርብ ዜና


Loading...