Image placeholder
የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የ90ቀናት ተግባራት ገመገመ።
By web admin | 2024-02-29

በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በቀጣይ 90 ቀናት በሚከናወኑ ተግባራት እቅድ የክፍለ ከተማና ወረዳ አጠቃላይ አመራር ጋር ውይይት አደረገ።

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም  ሙላቱ እንደገለፁት ገቢ አሰባሰብ ስራችን፣የወጣቶች ስራ እድል፣የከተማ ግብርናና ሌማት ቱሩፋት፣የኑሮ ውድነት፣ትምህርት ለትውልድ፣ኢትዮጵያ ታምርትን ንቅናቄ በቀጣይ 90 ቀን በልዩ ትኩረት የምንሰራቸውና የርብርብ ማዕከል እንደምናደርግ አቅጣጫ ተቀምጧል

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ወልዴ ወገሴ እንደገለፁት አመራሩ በቀጣይ 90 ቀናት በጠንካራ የአመራር ስምሪት ተልኮዎች ሊፈፅም ይገባል ብለዋል።

የክፍለ ከተማው ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ይከበር ስማቸው በበኩላቸው መደበኛ የመንግስትና የፓርቲ ስራዎችን በማቀናጀትና በልዩ ሁኔታ በተቆጠሩ የ90ቀን እቅድ ላይ ርብርብ በማድረግ የህዝባችንን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።

የቅርብ ዜና


Loading...