Image placeholder
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ወጣቶች ሊግ ጽ/ቤት በበጋ ወራት ያደሰውን የአቅመ ደካማ ቤት አጠናቆ የከተማ የሱፐርቪዥን ቡድን ፣የክፍለ ከተማ አስተባባሪዎችና የወረዳ አመራሮች በተገኙበት አስረክቧል።
By Belay | 2024-06-25

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ወጣቶች ሊግ ጽ/ቤት በበጋ ወራት ያደሰውን የአቅመ ደካማ ቤት አጠናቆ የከተማ የሱፐርቪዥን ቡድን ፣የክፍለ ከተማ አስተባባሪዎችና የወረዳ አመራሮች በተገኙበት አስረክቧል።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ይከበር ስማቸው በሰው ተኮር ስራዎቻች የአቅመ ደካማ ቤተሰቦችን ቤት ዕድሳት በማድረግ ኢትዮጵያዊ የመረዳዳትና የመደጋገፍ እሴቶችን የተግባር ማሳያ በመሆኑ በዚህ ክረምትም ሁሉም ህብረተሰብ የበጎ ፍቃድ አገልግሎትን አጠናክሮ መስራት ይኖርብናል ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች ሊግ ፅሀፊ አቶ አንሙት አበጀ በበኩላቸው ለሱፐርቪዥን ስራ ወደ ጉለሌ በመጡበት ስዓት የወጣቶችን የነቃ ተሳትፎ በዚህ መልኩ በማየታቸው እንዳስደሰታቸው ገልፀው ወጣትነታችንን ለበጎ አላማ መጠቀም አለብን ብለዋል።

የክፍለ ከተማው ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ጽ/ቤት ወጣት ደሱ ሳህሌ በኩላቸው የየአካባቢው ወጣቶችና በጎ ፍቃደኞችን በማስተባበር የአቅመ ደካሞችን ቤት ዕድሳት አገልግሎት በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።

በዕለቱ "የብልጽግና ትውልድ!" በሚል የክረምት የበጎ ፍቃድ የአቅመ ደካማ ቤት እድሳት ያስጀመሩ ሲሆን በወጣቶች ርብርብ በአጭር ጊዜ በማጠናቀቅ እንደሚሰራ ተነግሯል።

የቅርብ ዜና


Loading...