Image placeholder
የኑሮ ውድነትን ለመቋቋም፣ በምግብ እራስን ለመቻል እና የአመጋገብ ባህል ለማሳደግ ብልጽግና ፓርቲ የከተማ ግብርናን ዋና አቅጣጫ አድርጎ በመስራቱ ለውጦችን ማምጣት ተችሏል:- አቶ ይከበር ስማቸው የጉለሌ ክ/ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊ
By Belay | 2023-08-27

በዘርፉ ጠንክረን ከሰራንና ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ከቻልን በከተማ ውስጥ የስራ እድል ፈጠራ ከማሳደግ በተጨማሪ ከራስ አልፎ ለሌለው መትረፍ የምንችልበትን አቅም እየፈጠርን እንችላል ሲሉ አቶ ይከበር ስማቸው በክ/ከተማው አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ጽ/ቤት በ2015 በጀት አመት ሪፖርት ግማገማ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ባደረጉበት ወቅት ገልጸዋል።

በተጨማሪ የከተማ ግብርና ትልቁ ጥቅሙ ከሸማችነት ወደ አምራችነት መቀየርና ለሌላውም መትረፍ ከመሆኑ አንጻር በጓሮ አትክልትና የእንስሳት እርባታ ለውጦች ማምጣት ተችሏል ሲሉ የክ/ከተማው አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ፍራኖል ሞሲሳ ገልጸዋል።

ህብረተሰቡ ከእለት ወደ እለት የግንዛቤ መጠኑና ምርታመነቱ እያደገ መምጣቱን አቶ ፍራኖሎል ገልጸው በዘርፉ ጥቅምና አስፈላጊነት አንጻር በሁሉም ባለድርሻ አካላት የተደራጀ አቅም የላቀ ስራ መሠራት እንዳለበት አሳስበዋል።

በመጨረሻም በበጀት አመቱ የተሻለ አፈጻጸም ላላቸው ተቋማትና ግለሰቦች እውቅናና ሽልማት ተሰጥቷል።

የቅርብ ዜና


Loading...