Image placeholder
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ከ36 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው መስሪያ ሼዶች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል፤
By Belay | 2023-08-04

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር መስሪያ ሼዶቹን መርቀው ለአገልግሎት ክፍት ባደረገቡበት ወቅት እንዳሉት፣ በአዲስ አበባ ከተማው የወጣቶችንና የሴቶችን ፍትሃዊ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ነው ያሉ ሲሆን ዛሬ በከተማ ደረጃ በሁሉም ክ/ከተሞች የመስሪያ ሼዶችን አስመርቀን እያስተላለፍን መሆኑ አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል።

አፈ-ጉባኤዋ አክለውም፣ የተመረቁት ሼዶች የነዋሪውን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡና ህዝቡ ያነሳውን ጥያቄ የሚመልሱ ከመሆናቸውም በላይ የዜጎችን የመስሪያ ቦታ ችግር የሚቀርፉ ፣መንግስት ለህዝቡ ቃል የገባውን በተግባር ያረጋገጠባቸው ናቸው ብለዋል።

የቅርብ ዜና


Loading...