Image placeholder
የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ለዓለም የሴት ቦክስ ሻምፒዮኗ 200 ሺህ ብር ከወረዳና ከክፍለ ከተማ አጠቃላይ አመራሩ በማሰባሰብ ድጋፍ አደረገ።
By Belay | 2024-06-25

የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ለዓለም የሴት ቦክስ ሻምፒዮኗ 200 ሺህ ብር ከወረዳና ከክፍለ ከተማ አጠቃላይ አመራሩ በማሰባሰብ ድጋፍ አደረገ።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ነዋሪ የሆነችው ምክትል ሳጅን ቤተልሔም ገዛኸኝ ኢትዮጵያን ከ30 ዓመት በኋላ በቦክስ ሻምፒዮና በማድረግ በዓለም መድረክ ስሟን አስጠርታለች በደቡብ አፍሪካ በሚደረገው የቦክስ ውድድር ላይ በመሳተፍ ላይ እያለች በደረሰባት የትከሻ ውልቃት ደርሶባት ሕመሟን ተቋቁማ የብር ሜዳሊያ አስገኝታለች።

በድጋፍ ስነ ስርዓቱ ላይ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ እንደናገሩት የክፍለ ከተማችን ነዋሪ ሆና ሀገራችንን በተለያዩ መድረኮች በመወከል የተወዳደረችው ም/ ሳጅን ቤተልሔም ገዛኸኝ የትከሻ ውልቃት ዜና በማህበራዊ ሚዲያ የሰማን ቢሆንም የክፍለ ከተማውና የወረዳ አመራሮች በማስተባበርና በመሰብሰብ የ200 ሺህ ብር ድጋፍ አድርጓል ብለዋል።

ምክትል ሳጅን ቤተልሔም ገዛኸኝ ከክፍለ ከተማው አስተባባሪ ኮሚቴ እጅ የተዘጋጀላትን የ200 ሺህ ብር ቼክ ተረክባለች።

የቅርብ ዜና


Loading...