Image placeholder
የአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ቁጥጥርና ፈቃድ ባለስልጣን በክረምት በጎ ፈቃድ መርሃ ግብር በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ያሳደሳቸውን 8 የአቅመ ደካማ ቤቶችን ቁልፍ አስረከበ።
By Belay | 2023-08-04

በጎነት_ለዘላቂ_አብሮነት!!

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከክፍለ ከተማው ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ጋር በጋራ በመሆን ስምንት የአቅመ ደካማ ቤቶች በማደስ በዛሬው ዕለት የቁልፍ ርክክብ አካሄዷል።

በቁልፍ ርክክቡ ላይ የተገኙት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተስፋዬ ኦሜጋ እንደተናገሩት በክፍለ ከተማው የ300 የአቅመ ደካማ ቤቶችን ለማደስ በዕቅድ የተያዘ ሲሆን ከነዚህም 10 የሚሆኑ የአቅመ ደካማ ቤቶችን የአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ቁጥጥርና ፈቃድ ባለስልጣን ለማደስ በገባው ቃል 8 የሚሆኑትን በዛሬው ዕለት አስረክቦናል ይህ ተግባሩ ለሌሎች ሴክተር መስሪያ ቤቶች አርዓያ የሚሆን ተግባር በመሆኑ ሊበረታታ ይገባል ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ምትኩ አስማረ በበኩላቸው የበጎ ፈቃድ ተግባር በንፁህ ህሊና የሚሰራ በመሆኑ መስሪያ ቤታችን ማህበራዊ ኃላፊነቱን በሚችለው አቅም ለዚህ በጎ ዓላማ የበኩሉን አስተዋፅዖ በማድረግ ለዛሬው የቁልፍ ርክክብ ላይ ደርሰናል ብለዋል።

የክፍለ ከተማው ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኃይለ ማርያም አባይነህ በበኩላቸው የአቅመ ደካማቤቶች እድሳት የዜግነት ግዴታችንን እምንወጣበት መንገድ መሆኑን በመገንዘብ ወደ ተግባር የገባንበት መሆኑን እና ወደተሻለ ስራ የመጎዝ እና እቅዳችንን የምናሳካ መሆኑን ገልፀዋል።

የቤት ዕድሳቱ ተጠቃሚዎ ከዚህ በፊት በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ እንደነበሩ ገልጸው በአሁኑ ሰዓት ምክር ቤቱ ችግራቸውን ተመልክቶ ለማደስ እንቅስቃሴ በመጀመሩ ደሰታቸውን በመግለጽ ምስጋናቸው አቅርበዋል።

የቅርብ ዜና


Loading...