Image placeholder
ብዝሀ ቋንቋ ብዝሀ ማንነት ባለባት ሀገር ገዥ ትርክትን በመፍጠር ብሔራዊነትን ማፅናት ያስፈልጋል ።
By Belay | 2024-06-25

ብዝሀ ቋንቋ ብዝሀ ማንነት ባለባት ሀገር ገዥ ትርክትን በመፍጠር ብሔራዊነትን ማፅናት ያስፈልጋል ።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት በወረዳ ደረጃ ሲያካሂድ የቆየውን የማስ ስፖርት የንቅናቄ መርሀ ግብር በዛሬው ዕለት በክፍለ ከተማ ደረጃ አካሂዷል።

በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የዕለቱ የክብር እንግዳና የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ በላይ ደጀን ጉለሌ ለከተማችንም ለሀገረም በስፖርቱ ዘርፍ እያበረከተ የሚገኝ ክፍለ ከተማ ነው ያሉ ሲሆን ለብሔራዊነትና አሰባሳቢ ትርክት ወጣቱ የበኩሉን ድርሻ መወጣት አለበት ብለዋል።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ወልዴ ወገሴ በበኩላቸው እንደ ሀገር ብልፅግና ፓርቲ ከተመሰረተ ጀምሮ ለኢትዮጵያ ትንሳኤ ለመጪው ትውልድ መፃኢ ዕድል ምቹ ሁኔታ መፍጠር ታሳቢ ያደረገ ሁለተናዊ ስራ እየሰራ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ህዝብ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች ለመመለሰ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በማቋቋም ወደ ተግባር በመግባት ስራ ላይ ነው በማለት ለገዥ ትርክትና ብሔራዊነት የክፍለ ከተማችን ነዋሪዎች የፓርቲው አባላት ወጣቶች ሴትች በዛሬው ማስ ስፖርት ላይ የተሳተፋችሁ የስፖርት ቤተሰቦች የበኩላችሁን ድርሻ እንድትወጡ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ይከበር ሰማቸው በበኩላቸው ከወረዳ ጀምሮ ለዛሬው መድረክ ጭምር ልዩ ትኩረት ለሰጡ አካላት በፓርቲው ስም አመስግነው ከብሔራዊነት ውጪ ሌላ የተሻለ አማራጭ ስለሌለን አሰባሳቢና ገዥ ትርክት ላይ በትኩረት እየሰራን የኢትዮጵያን ሁለተናዊ ብልፅግና ማረጋገጥ ይጠበቅብናል ብለዋል።

የቅርብ ዜና


Loading...