Image placeholder
መደበኛ የፓርቲና የመንግስት ስራዎችን በአግባቡ በመፈፀም ወደ ላቀ ውጤት ማሸጋገር ያስፈልጋል !!
By web admin | 2024-05-21

መደበኛ የፓርቲና የመንግስት ስራዎችን በአግባቡ በመፈፀም ወደ ላቀ ውጤት ማሸጋገር ያስፈልጋል !!

የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር መደበኛ የመንግስትና የፓርቲ ስራዎች አፈፃፀም ያሉበትን ደረጃ የወረዳ አስተባባሪና የክ/ከተማ አመራር ባሉበት ግምገማ አካሄዷል።

ተግባራትን በማስተሳሰር መምራት የብልፅግና አመራር መለያ እየሆነ በመምጣቱ በርካታ ውጤቶች እየተመዘገቡና የህዝቡ የመልካም አስተዳደር፣የልማትና የአገልግሎት ጥያቄዎች እየተፈቱ ይገኛልም ተብሏል። አስተዳደሩ በ90 ቀን እና በመደበኛ እቅድ የያዛቸውን የስራ ዕድል ፈጠራ፣ የሰው ተኮር ተግባራት፣ የከተማ ግብርና፣የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ፣የኑሮ ውድነት መከላከልና ተቋማትን ማዘመን፣የግብር ገቢ ማሰባሰብና የደረሰኝ ግብይትን ማጠናከርና መሰል ተግባራትን ወደ ተሻለ አፈፃፀም ለማምጣት ከመደበኛው እቅድ ላይ ቀንሶ እየሰራ እንደሆነም ተገልጿል።

በዋናነት በዛሬው ግምገማ ላይ የተነሳው ለሁሉም ተግባር መሳካትና ለሁለተናዊ ብልፅግና ጉዞ እውን መሆን የሰላምን ጉዳይ ማረጋገጥ የተጀመረውን የሰላም ሰራዊት ስምሪት ማጠናከርና በየቦታው የተበተነውን ፅንፈኛ ሀይል ወደ ከተማችን እንዳይገባና የስራ እንቅፋት እንዳይሆን በንቃት መስራትና እየታየ ያለውን የሰላም ውጤት ማስቀጠል ያስፈልጋል ተብሏል።

ከፓርቲ ስራዎቻችን አንፃር በቀሪ 2ወራት የታቀዱ እቅዶችን ወደ ስራ መለወጥና ለ2017 በጀት አመት የጠራ አባልና አመራር ይዞ ለመቀጠል በሁሉም ወረዳ የተጀመረውን የማጥራት ስራ አጠናክሮ ማስቀጠል ያስፈልጋል ተብሏል።

በመጨረሻም እያንዳንዱ ተግባራት በዝርዝር አተገመገመ በኋላ በቀጣይ በሚከናወኑ ወቅታዊና መደበኛ ተግባራት ዙሪያ አቅጣጫ ተቀምጧል።

የቅርብ ዜና


Loading...