![Image placeholder](images/2460520230804.jpg)
![Image placeholder](images/2460520230804.jpg)
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ፅ/ቤት በ2015 ዓ.ም በጀት አመት ከ55 ሚሊዮን ብር በላይ በመሰብሰብ የእቅዱን 122% ማሳካቱን ጽ/ቤቱ አስታውቋል።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት በሃብት አሰባሰብ እና በህዝብ ንቅናቄ ተሳትፎ በኩል የነበረውን የ2015 ዓ.ም አፈፃፀም ከፍተኛ በመሆኑ የአ.አ ከተማ አስተዳደር የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት የላቀ አፈጻጸም የምስጋናና የእውቅና ዋንጫና ሰርተፍኬት አበርክቶልናል።
እውቅናውና የላቀ አስተዋጽኦ እንዲመጣ ላደረጉ የክ/ከተማና የወረዳ አስተባባሪ አካላት;አመራሩና መላው የክፍለ ከተማችን ነዋሪዎች ላቅ ያለ ምስጋና በማቅረብ በቀጣይም ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ተጠይቋል።